ፕሮጀክት ፖውዝ
ህይወትዎ ቆምዋል ወይ?
ካሃገርዎ ሲፈናቀሉ ህይወትዎ በድንገት ተቀይርዋል ወይ?
ምን ተማሩ?
እንዴት እየመከቱት ነው?
ብአሁኑ ሰዓት የኮቪዲ 19 መስፋፋትን ለመግታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እራሳቸውን በየቤታቸው ነጥለው በሚገንኙበት ግዜ : ብዙ ከሃገራቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ብዙ ይሚያመሳስሉኣቸው እንድምታዎችን ማስተዋል ጀምረዋል ።እርስዎ ባለሞያ ኖት።ያልዎትን ልዩ ችሎታ ወይም ተሰጥኦ በማካፈል በአሁኑ ሰዓት የተነጥሎ መኖርን በመለማመድ ላይ የ ሚገኙ ሰዎችን ማገዝ ይችላሉ።
ፕሮጀክት ፖውዝ በቀጥታ ሁሉንም የሚያሳትፍ ክፍት የድህረ -ገጽ ማህደር ሆኖ የተለያዩ ከሃገራቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ታሪኮችን ፣ቃሎችን፣ተመኩሮዎችን እና ልዩ ችሎታዎች ያካተተ ነው።ያልዎትን ልዩ ችሎታ በተለያየ ምንገድ ማካፈል ይችላሉ። በስእል፣በቅብኣ፣በንግግር፣በጽሑፍ፣በተውኔት……….
ስእል፣ቅብኣ – ፎቶ በማንሳት
ንግግር፣ቃለመጠይቅ፣ዘፈን – በድምፅ ኖት ወይንም በዋትስኣፕ በመቅዳት
ተውኔት፣እንቅስቃሴ፣ውዝዋዜ – ቪድዮ በመቅዳት
ጽሑፍ – ኖት በመጻፍ ወይ ፎቶ በማንሳት
……በዋትስኣፕ ወይ በቫይበር +447506 663089 ይለላኩልን።
ተለቅ ላሉ ሰነዶች በ [email protected]ይላኩልን።
የደረሱንን ይዞታዎች በግንቦት ወር መጨረሻ ኣካባቢ ብድህረ ገፃችን ለመልቀቅ እንደ መድብ ተይዝዋል። ከዛ በመነሳት ፕሮጀክቱ እያደገ እንደሚሄድ ባለሙሉ ተስፋ ነን።
ፕሮጀክት ፖውዝ በ ህዮማን ፎር ራይትስ ኔትዎርክ እና በ ፒስፋል ቦርደርስ የተዘጋጀ ፕሮጀክት ነው።